አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ ለማድረግ የገባነው ቃል በፍጥነትና በጥራት እየተተገበረ ነው!!

ዛሬ የስምምነት ፊርማ የተከናወነላቸው የከተማችን አዲስ አበባ ዘመናዊና አዲስ ዘመን ፈንጣቂ መንገዶች እውነታዎች !!

• በአጠቃላይ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መንገድ ነው፡፡

• ከ15 – 30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸውን 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ ያካተተ ነው፡፡

ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተ ዲዛይን የተሰራለት ነው፡፡

• የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በመከናወን ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡

• ከ2.4 – 4 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አለው፡፡

• 2 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ አለው፡፡

• 9 የሳይክል ማቆሚያና 3 የሳይክል መከራያ ቦታዎች አሉት፡፡

• ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ የብልህ የትራንስፖርት ስርዓት አለው።

•10 የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ ሲሲቲቪ ካሜራዎች አሉት።

• 2 ቦታዎች ላይ ዲጂታል የትራፊክ መቁጠሪያዎች አሉት።

• ቅፅበታዊ የአውቶቡስ መረጃ ማግኛ ስርዓቶች አሉት።

• ኦፕቲክ ፋይበርና ዲጂታል ዋይፋይ ባክአፕ አለው።

• መዝናኛ ቦታ ተካቷል።

የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ማሻሻያ

• የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT B-7) አካቷል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

Leave a Reply