ቢሮው በመዲናዋ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለውን ስራ ገመገመ።

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ስራና የመጣውን ውጤት የቢሮው አመራሮች ከቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና ከከተማ አውቶብስ አመራሮች ጋር ዛሬ በጋራ ገምግሞል።

በግምገማውም የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ቢሮው ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣንና ከከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በቅንጅት እየሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑንና የሰልፍ ቆይታውን መቀነሱን ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አከባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ መፍታት እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ አመራሩ ወርዶ እየደገፈ ያለበት መንገድና የመጣው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልፀው፤ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ያሉንን የትራንስፖርት አማራጮች በሙሉ አቅም መጠቀም እንደሚያስፈልግ በአንክሮ ገልፀዋል።

Leave a Reply