በፒያሳ እና አካባቢው እየተከናወነ ከሚገኘው የመንገድ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ በግንባታ ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ኮሪደር የልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በፒያሳና አካባቢው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ቀደም ሲል የመንገዱን መዘጋት በተመለከተ መረጃ ቢሰጥም አሁንም አሽከርካሪ ዎች ወደ ግንባታ ቦታው እየመጡ በግንባታ ስራው ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ፖሊስ አስታውቆ አሽከርካሪዎች በመረጃው በመጠቀም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተጠይቋል ።

በዚህም መሰረት

• ከጊዮርጊስ አደባባይ በእሳት አደጋ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከቅድስተ ማርያም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

• ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ቱሪስት እና ወደ ቅድስተ ማርም

• ከእሪ በከንቱ (ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም) ወደ ደጎል አደባባይ እንዲሁም

• ከደጎል አደባባይ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ በሚወስዱት መንገዶች መግባት እና መንገዶቹን ለጊዜው መጠቀምም ሆነ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም የማይቻል በመሆኑ አሽከርካሪዎች ከእነዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply