በአዲስ አበባ የትራፊክ በጎ ፍቃደኞች የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ (ሰኔ 16/2016 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎ የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እና የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የትራፊክ በጎ ፍቃደኞች የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀመሩ።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ በዘንድሮ ዓመት በመንገድ ደህንነት ዘርፍ የሚሳተፉ በጎ ፍቃደኛ የከተማዋ ነዋሪዎቸና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ፤ በተለይ አሁን እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት የትራፊክ ፍሰቱን የሚቀንስ ቢሆንም ቀሪ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ከመንግስት ባለፈ የማህበረሰቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ብለዋል ።

በተለይ ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አሽከርካሪዎች የመኪናቸውን ደህንነት መከታተል እና ለበጎ ፍቃደኞች መታዘዝን ባህል ማድረግም መለመድ አለበት ሲሉም አክለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በመንገድ ደህንነት ዘርፍ ከ 6 ሺ 500 በላይ በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉም በመድረኩ ተገልጿል።

የዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

@ AMN

Leave a Reply