በአዲሱ የሪፎርም አደረጃጀት ቢሮ ላይ ለተመደቡ አዲስ የስምሪትና የቁጥጥር ሰራተኞች የአገልግሎት አሰጣጡን መስክ በመውረድ የተግባር ስልጠና ወሰዱ።

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአዲሱ ሪፎርም በምደባ ከሌላ ተቋም ለመጡ 76 የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ተቆጣጣሪ ሠራተኞች ወደ ስራ ለማስገባት ሲሰጥ የነበረው የቲዎሪ ስልጠና ተጠናቆ የመስክ ላይ የተግባር ስልጠና ሰልጣኞች ወስደዋል።

በመስክ የተግባር ላይ ስልጠናውም አዳዲስ ሠራተኞቹ ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ለስራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን፣ አገልግሎት አሰጣጡን፣ የመረጃ አያያዝና ሌሎች በስራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ በማወቅ አገልግሎት አስጣጡን የተሻለ ለማድረግና ከነባሮች ልምድ በመቅስም በተግባር የሚያውሉ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጠር ነው፡፡

የመስክ የተግባር ላይ ሰልጣኞችም ቢሮው ለአራት ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ስለ በቢሮው ስለሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የስምሪት ቁጥጥር ባለሙያ ተግባርና ኃላፊነት ጠንቅቀን እንድናውቅ እንዲሁም በአገልጋይነት መንፈስ ወደ ስራ እንድንገባ ስንቅ ይሆናል ብለዋል።

Leave a Reply