በህገወጥ የባለ 3 እና ባለ 4 እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ እየተደረገ ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሎል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም)

የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠባቸው የሚገኙ 8 የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየተደረገ ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ ቀጥሎል።

ቁጥጥሩም መዋናነት ህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ይስተዋልባቸዋል ያላቸውን ቦታዎች በጥናት በመለየት መሆኑን ስራውን በበላይነት እያስተባበሩ የሚገኙት የቢሮው የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ገልፀዋል።

ከስምሪት መስመር ውጭ በሚሰሩ፣ ለባጃጅ ባልተፈቀደ መንገድ የሚያሽከረክሩ፣ የመስመር ታፔላ የሌላቸው፣

ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ (መንጃፍቃድ) ሳይዙ የሚያሽከረክሩና ከተቀመጠው ታሪፍ በላይ በማስከፈል የመልካም አስተዳደር ችግር በፈጠሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው ኮልፌ ቀሪኒዮ፣ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ፣ ንፋስ ስልክ፣ የካ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማና ጉለሌ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከፖሊስ፣ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፣ ሰላምና ፀጥታ፣ ደንብ ማስከበርና የፀጥታ ግብረ ሃይል የጋራ ቅንጅት በመፍጠር ህገወጦችን ወደ ህጋዊነት ለማምጣት እየተሰራ እንደሚገኝና የእርምት እርምጃ በመውሰድ ተጠያቂ የማድረግ ስራም እየተሰራ ይገኛል።

Leave a Reply