ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መቻሉን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የካቲት 22/2016ዓ.ም)

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ባለው ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ባለፈው የግማሽ በጀት ዓመት በርካታ አበረታች ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት አሳውቋል፡፡

በግምገማው በግማሽ አመቱ የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማሻሻል እና የአገልግሎት ጥራቱን ለመጠበቅ ትኩረት በመሰጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ መሰራቱ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

የንፋስ ስልክ ፅህፈት ቤት ትራንስፖርት ስራ አሰኪያጅ አቶ ሰብስባቸው መንግስቴ ባለፉት ስድስት ወራት የትራንስፖርት ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት፣ ብልሹ አሰራሮችንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍታት እና የአቅም ማጎልበቻ ስራዎችን በማጠናከር ከባለድርሻና ከቅርንጫፉ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል ብለዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ፅህፈት ቤት የትራፊክ ግንዛቤ ማስጨበጫ ኃላፊ ኢኒስፔክተር ተፈራ ገንዘቤ በበኩላቸው ቢሮውና ተጠሪ ተቋማቱ አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር መገምገሙ ለተሻለ ውጤት ያግዛል ብለዋል።

በመጨረሻም በበጀት አመቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እና በአፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑ ሰራተኞች የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ።

በውይይቱም የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራፊክ ፖሊስ፣ ሰላምና ፀጥታ፣ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፣ ከከተማ አውቶብስ፣ ከደንብ ማስከበር፣ ከተራ ስከባሪዎች፣ የሼድ ፅዳት ሰራተኞች፤ ከሃይገርና ታክሲ ማህበራት አመራሮች እና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply