ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው አካባቢዎች ርቀትን መጠበቅ ይገባል፡፡

ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው አካባቢዎች ርቀትን መጠበቅ ይገባል፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012፤ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እጅ መታጠብን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ከዚህ ውስጥ ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች በተለይ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠቀም ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከማንኛውም ሰው በ1 ነጥብ 8 ሜትር ራስን ማራቅ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ርቀትን የመጠበቁ ዋና አላማ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እና ለዓለም አቀፉ የጤና ስርዓት ድጋፍ ለሚፈልጉት ተጨማሪ ጊዜን ለመስጠት ነው ተብሏል።

ሆኖም በአዲስ አበባ በትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችና በፋርማሲዎች አካባቢ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ተሰልፈው ታይተዋል።

በመሆኑም ስርጭቱን ለመቀነስ እና በቫይረሱ ላለመያዝ አጠገብዎ ካለው ሰው ሊኖርዎት የሚገባውን ርቀት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል መልዕክታችን ነው።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ዳቦ ቤትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲሁም በታክሲ እና አውቶብስ ፌርማታዎች ላይ መሰል ሰልፎችን እና መጠጋጋቶችን ማስወገድም ይገባል።

Leave a Reply