#ለባለ_ሶስት እና አራት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች/ ባለንብረቶች በሙሉ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል፡፡

Leave a Reply