የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አራዳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ ሲሰጥ ነበረውን የአውቶብሶች መነሻ መጫኛ የተርሚናል ቦታውን ለውጥ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 06፤ 2015 ዓ.ም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አራዳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ ለረጅም ጊዜ ሲገለገልበት የነበረውን የአውቶብሶች መነሻ መጫኛ የተርሚናል ቦታውን ለውጥ አደረገ፡፡

ከፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ መነሻቸው የነበሩ ዘጠኝ (9) የአንበሳ አውቶብስ መስመር ቁጥር 03፣ 05፣ 14፣ 37፣ 59፣ 70፣ 103፣ 107 እና 123 እንዲሁም ስድስት (6) የሸገር አውቶብስ ከሚኒሊክ አደባባይ ወደ ሳሪስ አቦ፤ ጎፋ ኮንዶሚኒየም፤ ጀሞ፤ አየር ጤና፤ ካራ ቆሬ እና ቤቴል አለም ባንክ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አውቶብሶች መነሻና መጫኛ የተርሚናል ቦታውን ከዛሬ 06/04/2015 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ኮካ መናፈሻ አካባቢ የተዘዋወረ መሆኑን እና ህብረተሰቡ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ተቀያሪ ተርሚናል ላይ እንዲጠቀም ሲሉ የአራዳ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስባቸው መንግስቴ ገልፀዋል፡፡

የመጫኛና ማውረጃ ቦታው ለውጥ መደረግ ያስፈለገ በት ምክንያት የቀድሞ ቦታው አደባባይ ላይ በመሆኑ ለህዝብ ትራንስፖርት ተገልጋዩች ምቹ ባለመሆኑና ለትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።

በተጨማሪም ወደ ተግባራዊነቱ ለመግባት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ከአዲስ አበባ ማዕከላዊ ትራፊክ ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት፣ ከአራዳ ትራፊክ ፖሊስና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን መጫኞና ማውረጃ ቦታው በመቀየሩ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖረውን ፋይዳ ጥናት መደረጉም ተጠቀሟል፡፡

በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተክሌ ካሰዬ የህዝብ ትራንስፖርት መጫኝና ማውረጃ ቦታዎች ለትራፊክ ፍሰቱና ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ምቹና ምልልሱንም የሚጨምር እንዲሆን ኤጀንሲው ከቢሮው ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነና በቀጣይም የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድግ

ይስራል ብለዋል::

Leave a Reply