300 ረዳት የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች የመልካምነት እና የበጎ ፈቃድ ስራን ተቀላቀሉ

(ግንቦት 05/2015 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ 300 ረዳት የተማሪ ትራፊክ አስተባባሪዎችን አስመረቀ፡፡

ኤጀንሲው ባለፉት አምስት ሳምንታት የተማሪዎቹን የትምህርት ጊዜ በማይነካ ቅዳሜ እና እሁድ ለትራፊክ አደጋ ተጋለጭ ከሆኑ 30 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 300 ተማሪዎች በመሰረታዊ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትና በማስተናበር ስራ በማሰልጠን አስመረቃቸው፡፡

በምርሀ ግብሩም የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጀንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ለረደት የተማሪ የትራፊክ አስተናባሪዎች የመልካምነት እና የበጎ ፈቃድ ስራን በዚህ ዕድሜያችሁ መቀላቀላችሁ ነገ ለሀገራችን ለምታበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ የሞራል እና የስራ ስንቅ እንደሚሆን ገልጸው፤

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤን ለማሳደግ በኤጀንሲው ከሚሰሩ ስራዎች የመንገድ ደህንነት በመደበኛ የትምህር ካሪኩለም ተካቶ እንዲሰጥ ኤጀንሲው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በቅንጅት በመስራቱ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ የመንገድ ትራፊክ ፍሰትን በማስተናበር መደበኛ የትራፊክ ፖሊሶችን እና የኤጀንሲውን የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንደሚያግዙና በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚደርስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋፅዖ አንደሚኖራቸው በምርቃት መርሀግብሩ ተገልጿል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት የስራ ኃላፊዎች፣ ከትምህርት ቢሮ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዕለቱ የክብር እንግዳ አትሌት ቃልኪዳን ተሳታፊ ሆነዋል።

Leave a Reply