የጭነት አቅማቸው ከ7 ቶን በታች የሆኑ ተሽከርካሪዎች የጭነት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማውጣት እንደሚገባቸው ተገለፀ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ነሐሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም)

በመዲናዋ የጭነት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ከ7 ቶን በታች የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች በተቀመጠው የኦፕሬተርነት ፈቃድ ማረጋገጫ መስፈርት መሰረት ፈቃድ እንዲያወጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች የኦፕሬተርነትና የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እየሰጠ መሆኑ ቢታወቅም፤ በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ተሽከርካሪዎች ፍቃድ ሳይኖራቸው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል፡፡

ስለሆነም ከ7 ቶን በታች የመጫን አቅም ያላቸው አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንድትወስዱ ቢሮው ያሳስባል።

Leave a Reply