የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የፋይናንስ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በበጀት ዓመቱ ውጤታማና የተሳካ አፈፃፀም በማስመዝገብ ገቢ በመሰብሰብ፣ ጥራቱን የጠበቀ የኦዲት ሪፖርት በማቅረብ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት በዕቅድ በማከናወን እና ውዝፍ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን በመቀነስ ላይ በተሰሩ ተግባሮች ከቁልፍ 13 የከተማ አስተዳደሩ ባለበጀት ሴክተር ተቋማት መካከል የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቡ በአንደኝነት ደረጃ ተሸላሚ ሆኖል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ወልዳይ ገ/ሚካኤል ቢሮው ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ለልማት እንዲውል ለማድረግ ከፋይናንስ ቢሮ ጋር በቀጣይም በቅንጅት እንደሚሰራና የተሰጠውም እውቅና አበረታች ነው ብለዋል።

የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር የማጠቃለያ አፈፃፀም ግምገማና የዕውቅና መድረክ ላይ ነው።

Leave a Reply