የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም)

በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግና በቢሮው የተደረገውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ጋር ዛሬ በቢሮው አዳራሽ የስምምነት ሰነድ (Memorandum of cooperation) ተፈራርመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ቢሮው ያለውን ተቋማዊ ተልዕኮ ለማስፈፀም በጥናትና ምርምር ስራዎች፣ የትምህርት ዕድል ለማመቻቸት፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የአውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች፣ የማማከር አገልግሎትና የማህበረሰብ አገልግሎት ከዩንቨርስቲው ጋር በጋራ ለመስራት እንዲያስችል ስምምነቱ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ የጥናት ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሀም ደበበ ዩንቨርስቲው ከቢሮ ጋር በቅንጅት በጋራ በመስራት የከተማዋን የትራንስፖርት ዘርፍ በዋናነትም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የበኩላችን ሚና ለመወጣት እንሰራለን ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply