የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላትና ቁጥጥር ሰራተኞች ከመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ጀምሮ በተመረጡ ቦታዎችና ተርሚናሎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገለፀ፡፡

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ሐምሌ 18፤ 2016ዓ.ም)

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት እና የቢሮው የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞች ከመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ጀምሮ በተመረጡ ቦታዎችና ተርሚናሎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱንም መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት በተደጋጋሚ ከህብረተሰቡ በሚነሱ ጥቆማዎች እና ቅሬታዎች መነሻነት እንዲሁም የትራንስፖርት ቁጥጥር ስርዓቱንና አቅርቦቱን ለማጠናከር ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎች ከሰኞ እስከ ዓርብ እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችም ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው አስተያየትና ጥቆማ በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞች፣ ትራፊክ ፖሊሲ አባላት እንዲሁም በአካል በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ወይም በነፃ የስልክ መስመር 9417 የአጥፊ አሽከርካሪውን ታርጋና ሰዓት በመያዝ ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ቢሮው ጥሪውን ያስተላፋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply