የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በተማሪዎች የትራንስፖርት አጠቃቀም ዙሪያ ላይ ውይይት አደረገ፡፡

የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ በከተማችን ላይ ያለውን የመንገድ ፍሠት ለማስተካከል በትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን አውቶብስ መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን የተማሪዎች አውቶብስ የትምህርት ተቋማት የሚያመቻቹበት ሁኔታ ላይ መወያየት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተማሪዎች አውቶብስ በትምህርት ተቋማት መዘጋጀቱ ተማሪዎቸ በሠዓት ወጥተው በሠዓት እንዲገቡ የሚረዳ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ወደ ተግባር ለመግባት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ካሉ የትምህርት ተቋማት ጋር መወያየት እና የትምህርት ቤቶቹን ፍላጎት ማሰባሰብ እና አውቶቢሱን የሚገዙ ትምህርት ቤቶችን የመለየት ስራ የሚሰራ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከትራንስፖርት ቢሮ የመጡ የስራ ኃላፊዎች እና የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የበላይ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

Leave a Reply