ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቁትን የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመከታተል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የአተገባበር ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የከተማዋን ትራንስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የትራንስፖርት ስርዓት እንዲዘረጋ ለማስቻል ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቁትን የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ከባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል።

የውይይቱን ሰነድ ያቀረቡት የሞተር አልባ ትራንስፖርት ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ ግርማ ሳሙኤል እንደተናገሩት መመሪያው ከተማዋ ከተያየዘችው የልማት ጎዳና ጋር አብሮ መሄድ የሚያስችል ከባቢያዊ ተስማማነቱ የተረጋገጠ ሂደትን መከተል ያስችላል ።

በቀጣይነትም የባለድርሻ አካላትን አስተያየቶች እና ግብአቶች ተካትተውበት ለተግባራዊነቱ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply