ቢሮው የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶችን በተገቢው ለማስተዳደር በትኩረት እየሰራ ነው

(በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የትራንስፖርት ቢሮ፤ ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም)

በመዲናዋ የሚገኙ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶችን ለማስተዳደር እና ለመቆጣጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድኑር ሙዘይን እንደተናገሩት በተቋም ሪፎርም የመጡ አዳዲስ ሰራተኞችንና ነባር ሰራተኞችን በማሰልጠን የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን በተገቢው ምዝገባ በማድረግ ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር እንዲያስችል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሲስተም ስልጠና በሦስት ዙር 37 ለሚሆኑ የማዕከል እና የቅርንጫፍ ሙያተኞች ለአምስት ቀናት በየዙሩ በማሰልጠን አቅማቸውን በመገንባት ሀብቶቹን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም በዚህ ረገድ ቢሮው እየሰራ ያለውን ስራ የሚመለከታቸው ተቋማት እና የከተማዋ ህብረተሰብ በመደገፍ በኩል በተለይ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን በመንከባከብና በባለቤትነት በመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቶ መሀመድኑር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ 011666 33 74 ወይም በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply