*************
(ት/ማ/ባ ነሃሴ 18//2016 ዓ,ም)
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ቅ/ጽ/ቤቶች: የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል::
በስራ አፈጻጸማቸው ከ1_3 ደረጃን ያገኙት ቅ/ጽ/ቤቶች ልደታ:ለሚኩራ እና ቦሌ ሲሆኑ ከማእከል ዓላማ ፈጻሚ ዳይሬክቶሬቶች መካከል የቄጥጥርና ደንብ ; የመንገድ ደህንነት ምህንድስና እንዲሁም የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ዳይሬክቶሬቶች በደረጃ ከ1_3 ተቀምጠዋል::
በውጤት ደረጃቸውም መሠረት ኮምፒውተር: ዋንጫና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል::
ከደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች መካከል 1ኛ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች: ዳይሬክቶሬት: 2ኛ የአገልግሎት አሰጣጥ: የክትትል: ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት 3ኛ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት በየደረጃቸው የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል::
በተጨማሪም በማእከልና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከ1_3 ደረጃን የያዙ ባለሙያዎቾ የእጅ ሰዓትና ሰርተፊኬት ተሸልመዋል::
እንዲሁም ተቌሙን በሙያቸው ለደገፉ አርቲስቶች እውቅና ተሰጥቷል::



