የከተማ አስተዳድሩም የተሳለጠና አስተማማኝ የትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋት አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን የሚጨምር ወሳኝ መሆኑን አምኖ ሰፋፊ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ እነሆ ዛሬ በአገልጋይነት ቀን ከ16.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ 110 ዘመናዊና አዳዲስ አውቶቡሶችን ይዞ ለአዲስ አመት እንኳን አደረሣችሁ እያለ፣ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መጀመራቸውን ስናበስር ደስታ ይሰማናል።
እንኳን ደስ አላችሁ !!!
እነዚህ አውቶቡሶች አሁን የበለጸጉት አገራት እየተጠቀሙባቸው ያሉት አውቶቡሶች ደረጃ ያላቸው ዘመናዊ ናቸው፡፡
አውቶቡሶቹ ቀልጣፋ፣ ምቹ፣ ዘመናዊና ደህንነታቸው የተጠበቀ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው።ይህም ለከተማች ተጨማሪ መዘመንን ለነዋሪዎቿም የትራንስፖርት አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን የሚጨምር ይሆናል፡፡በዚሁ አጋጣሚ የዓለም ባንክን፣ የዩቶንግ ኩባንያን፣ ለስራው ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገው የገንዘብ ሚኒስቴርን እና የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንን በከተማ ነዋሪዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
አውቱቡሶቹን አገልግሎት አስጀምረን፣ እኛም ተገልግለናል፤ ዘመናዊና ምቹ መሆናቸው አረጋግጠናልን ።ጥንታዊውን የአንበሳ አውቶቢስ ብራንዱንም ይዝዉ እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
የዘመን ተሻጋሪዎች ብቻም ሳንሆን፣ ለአገራችን እና ለከተማችን ብልጽግና ባለቤቶች ሆነን እንትጋ፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!!
መልካም አዲስ ዓመት!
አመሰግናለሁ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ