የፊታችን እሁድ መስከረም 8/2015 ዓ.ም  መንገድ ለሰው  በሚል ስያሜ ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን ከማዘጋጃ ቤት በቴዎድሮስ አደባባይ ቸርችል ጎዳና እና ከወሎ ሰፈር እስከ ኡራኤል ባለው መንገድ ላይ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ በተለያዩ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች ይከናወናል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ :-

========

፨ የብዙሃን የእግር ጉዞ እና የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፤

፨ የብስክሌት መንዳትና ልምምድ እንዲሁም ስኬቲንግ፤

፨ ሩጫ፣ የጎዳና ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ኤሮቢክስ፤

፨ በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ይከናወናሉ።

ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን ዋና አላማ ሞተር አልባ እንቅስቃሴ በማበረታታት:-

* የትራፊክ አደጋ የማይከሰትባት ከተማ መፍጠር፤

* ለኑሮ ምቹና ከብክለት የፀዳ ከባቢ አየር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም

* እንደ አጠቃላይ ጤናማ የአኗኗር ዘዴን መፍጠር

* አማራጭ የትራንስፖርት መንገድ ማበረታታት፤

ከቤተሰብዎ፣ ከስራ ባልደረባዎ እና ከወዳጅዎ ጋር መጥተው ይዝናኑ፣ ጤናዎን ይጠብቁ!

Leave a Reply