የየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መገናኛ ተርሚናል ውስጥ ህገ-ወጥ ንግድ እንዳይካሄድ እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 14/2016ዓ.ም) የየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በመገናኛ ተርሚናል ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የነበረውን ህገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ ከደንብ ማስከበር፣ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ከፖሊስና ከተራ ማስከበር ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን ችግሩን በመፍታት መቻሉን አሳውቋል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ የየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበባው ታከለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ችግሩን ለመፍታት በተርሚናሉ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት ፈጥሮና የኦፕሬሽን ስራ በመስራት ውጤታማ ስራ መምጣት ችሏል ብለዋል፡፡

ችግሩም በመፈታቱ በተርሚናሉ ሰላማዊ የሰዎች ዝውውር፣ የስርቆት ወንጀልን በመፍታት ህብረተሰቡ አገልግሎቱን በሰላምና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ማግኘት መቻሉንና የህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይካሄድ መደረጉን የየካ ትራንሰፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አሳውቀው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply