የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአውቶቢስ ተርሚናል እና የዓድዋ ፕላዛዎች ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የአውቶቢስ ተርሚናል ተገልጋዮችን ከጸሃይ እና ከዝናብ ከመታደግ በተጨማሪ፣ የተሳፋሪዎችን ደህንነት የበለጠ ለማስጠበቅ የሚያስችል የደህነት ካሜራ የተገጠመለት እና የሰዎች ማረፊያ የተካተተበት ነው።

የዓድዋ ፕላዛዎች የአዲስ አበባ ህዝብ ምን ያህል የጋራ መገልገያዎችን እና መዝናኛዎች እንደሚፈልግ የሚያመለክትና የህዝብ ፍላጎት የሚያሳይ ነው። በክፍያ ወደሚገባባቸው የመዝናኛ ቦታዎች ከፍለው መግባት የማይችሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች እንደዚህ ባሉ የጋራ መገልገያ ቦታዎች መጥተው መዝናናት እና መገልገል ሲችሉ መመልከት ደስ ይላል።

በኮሪደር ልማት ይህን የህዝባችንን ከፍተኛ ፍላጎት በመገንዘብ በርካታ ፕላዛዎችን ፣ መዝናኛዎችን ፣ የአውቶቢስና የታክሲ ተርሚናሎችን እንዲሁም ፓርኪንጎችን አካትተን በመስራት ላይ እንገኛለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Leave a Reply