(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም) የኮልፌ ቀራኒዮ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ወረዳ 07 የሚገኘው ኮልፌ የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከል የሚወስደው መንገድ ከአምስት መስመሮች መነሻ ያደረገ አዲስ የትራንስፖርት አገልግሎት በዛሬው እለት መስጠት ጀመረ።
የኮልፌ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ደሱ አሰፋ የገበያ ማዕከሉ አሁን ያለውን የህዝቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀው፤ ወደ ገበያ ማእከሉ ለሚሄዱ ተገልጋዮች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በ5 መስመሮች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልፀዋል።
ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጀምሮ ማህበረሰቡ እንዲሁም ነጋዴዎች የትራንስፖርት ይመደብልን ጥያቄዎች ሲነሳ የነበረ ሲሆን አገልግሎት መጀመሩ የሚነሱ ጥያቄዎችን የፈታና ማህበረሰቡ ትኩስና ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በቀላሉ ቦታው ድረስ ለመሔድ እንዲያገኝ ያግዛል።
የትራንስፖርት አገልግሎቱ መነሻቸውን ከአየር ጤና ፣ ከቤቴል፣ ከየሺ ደበሌ፣ ከጦርሀይሎች፣ ከአለም ባንክ በማድረግ የገበያ ማዕከሉ ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።
በቀጣይም የትራንስፖርት አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በአንፎ (መቶ አምስት) አሸዋ ሜዳ _ጉጄ_ኬላ ፣ በሻቃ ሞል_ቡራዩ ማርያም ፣ ካራ_አጃንባ እና ፋኑኤል የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ እየሰራ ይገኛል።