የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ህጋዊ የባጃጅ ማህበራቶች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2015 ዓ.ም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክፍለ ከተማው በትራንስፖርት ቢሮ እውቅናና ፈቃድ ተሰጧቸው በህጋዊ መንገድ ተደራጅተውና ህጋዊ ሆነው ከሚሰሩ የባጃጅ ማህበራቶች ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ስብስባቸው መንግስቴ እንደገለፁት በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ተደራጅተውና በቢሮው እውቅና ፈቃድ ተሰጧቸው በክፍለ ከተማው እየሰሩ ያሉ 29 የባጃጅ ባለንብረቶች ማህበራት እንዳሉ በመግለፅ ከዚህ በፊት የነበሩ የአሰራር ስህተቶችንና ክፍተቶችን ለማስተካከልና በቀጣይ ስራን በተናበበና በተቀላጠፈ መልኩ በቅርበትና በቅንጅት ለመስራት ውይይቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በዉይይቱም በቀጣይ በሚኖረው የባጃጅ መስመር ዕድሳት ወቅት በተቋማዊ እና በአባልነት ደረጃ ማሟላት የሚገባቸውን ሊብሬ ኦሪጅናል ኮፒ የሚገናዘብ፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፣መንጃ ፍቃድ ፣ሶስተኛ ወገን ፣ቦሎና ንግድ ፍቃድ የመሳሰሉትን ተፈላጊ ሰነዶች አሟልተው መገኘት እንዳለባቸው እንዲሁም በተሰጣቸው ወይም በተፈቀደላቸው መስመርና ታሪፍ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ፤ በተጨማሪም በሌላ ህገወጥ ተግባር ላይ እንዳይገኙና በመመሪያው መሰረት ብቻ እንዲሰሩ የጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡

በውይይቱም በክፍለ ከተማው ዘርፉ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለቶች ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ፖሊስ እና ትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳተውበታል፡፡

Leave a Reply