የትራንስፖርት ቢሮ ከኮሎምቢያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የብስክሌት የደህንነት መሳሪያዎችን ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2015 ዓ.ም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የትራንስፖርት ቢሮ የብስክሌት ትራንስፖርትን በመዲናዋ ለማስፋፋት እየሰራ ላለው ስራ ከሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መካከል አንዱና ጠቃሚ የሆነውን የብስክሌት ደህንነት መሳሪያዎችን ከኮሎምቢያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በስጦታ ድጋፍ ተደረገለት፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ከኮሎምቢያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚስ ኤሊዮናራ ቤታናኩራ የብስክሌት የደህንነት መሳሪያዎቹን በዛሬው እለት ተረክበዋል፡፡

የደህንነት መሳሪያዎችቹ በአይነት 150 ሲሆኑ፤ መሳሪያዎቹም የጭንቅላት ቆብ (ሄልሜት)፣ አንፀባራቂ እና የጥገና መሳሪያዎችን የሚያካትቱ ናቸው። መሳሪያዎቹም በገንዘብ ሲተመኑ ከግምሽ ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

በተያያዘም በቀጣይ የብስክሌትና የብዙሀን ትራንስፖርት ዙሪያ ድጋፎችን ለማግኘት ውይይት አድርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የ10 አመት የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ በማዘጋጀት የሞተር አልባ ትራንስፖርት ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply