የቃሊቲ – ቡልቡላ – ቅሊንጦ አደባባይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሁሉም አቅጣጫ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በደቡባዊ አዲስ አበባ ክፍል እያስገነባቸው ከሚገኙ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት በሁሉም አቅጣጫ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡

አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀም ከ92.5 በመቶ ደርሷል፡፡

በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ያልተጠናቀቁ ቀሪ የተደራቢ አስፋልት ንጣፍ፣ የእግረኛ መንገድ ግንባታ፣ የቀለም ቅብ እና የመንገድ መብራት ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅም እየተሰራ ይገኛል፡፡

@የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

Leave a Reply