የቀደሙትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ግምገማ ስናጠናቅቅ ቀጣዩን ግምገማችንን በስራው ስፍራ ተገኝተን እንደምናካሂድ ቃል ገብተን ነበር። የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሶስት ወር መርሃግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል።

በቀጣይ ስራ ሀብት ቁጠባ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ በቀሪ ኮሪደሮች ስራዎቻችን ፈጣን እና ፈጠራ መር ልንሆን ይገባል። ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው።

ይህ ፕሮጀክት የሚራመደው በብዙሃን ትብብር ነው። ከጅማሮው በስራችን ባገኘነው በጎፈቃድ ምስጋና አቀርባለሁ። ይህም በእቅድ እና አፈፃፀም ላይ የታየውን ጥረታችንን እና መልካም ፈቃዳችንን የመጠነ ሆኖ ታይቷል።

በዚህ ከተማችንን ለተሻለ ለውጥ ለማብቃት በተደከመበት ታላቅ ስራ ሂደት ውስጥ በዜጎቻችን ላይ ፈጥረነው ሊሆን ለሚችል አለመመቸት ይቅርታ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያችን እንድትለወጥ በፅናት እንደምንሰራ በዚህ የኮሪደር ልማት ስራ ሂደትም ያሉ የዲዛይን እና የጥራት ክፍተቶችም ካሉ ማስተካከል እንደምንቀጥል እንድትተማመኑ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።

በግሉ ዘርፍ ያሉ አጋሮቻችንን ጨምሮ ትናንት ምሽት በጎዳናዎች ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን፤ በአጠቃላይም በዚህ ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Leave a Reply