የህፃናት፣ የሴቶች፣ የአረጋዊያን እና የአካል ጉዳተኞች መብትና ደህንነት ተጠብቆ የእኩል እድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፤

የከተማው አሰተዳደር 1ሺህ 629 አካል ጉዳተኞች የመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚ ሲያደረግ ለ362 አካል ጉዳተኞች ደግሞ የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ ማድረጉንም በዛሬው የምክር ቤት ሪፖርት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል።

ባለፉት 6 ወራት የሴቶችን ማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር በቁጠባ የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ፣ በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ 13,500 ሴቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታቅዶ 14,600 ማከናወን ተችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች በሪፖርታቸው በቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም 287,000 ህፃናት ትምህርትና እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ ታቅዶ 316,931 (ከ100% በላይ) ህፃናት ተጠቃሚ ሆነዋልም ብለዋል።

10ሺህ 800 ነፍሰ-ጡር ሴቶች፣ አጥቢ እናቶችና ሕፃናት የቀጥታ የአልሚ ምግብ ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነዋል ሲሉ ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል።

በየተቋሙ እና በመኖሪያ ቦታዎች 318 ምቹ የሕፃናት መጫወቻና መዝናኛ ስፍራዎች በመገንባት 18,482 ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 23,692 ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏልም ተብሏል፤

Leave a Reply