ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሺዬቲቭ ሽልማትን በማሸነፏ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሺዬቲቭ ሽልማትን በማሸነፏ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሺዬቲቭ ሽልማትን ካሸነፉ 10 የዓለማችን ከተሞች መካካል አንዷ ሆናለች፤ለዚህም እንኳን ደስ አለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

ከአምስት አህጉራትና ከ275 ከተሞች መካከል ተወዳድረው 10 ከተሞች የውድድሩ አሽናፊ መሆናቸውን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች፣የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አሸናፊዎቹ ሃገራትም፤ ኢትዮጵያ፣ ብራዚል፣ ህንድ፣ጣሊያን፣ አልባኒያ፣ ኒውዝላንድ፣ፖርቹጋል፣ ኮሎምቢያ፣ ኬንያና ሞዛምቢክ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

በዚህም አዲስ አበባ የ400 ሺህ ዶላር እንደምታገኝ ገልጸዋል፡፡

“ከተማችን ተሞክሮዋን በማስፋት ለመጪው ትውልድ እያስብን ዛሬ መስራታችን እንቀጥላለን” ሲሉም ገልጸዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባ አዳነች ይህ እድል እንዲገኝ አብረው ለሰሩ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት Bloomberg Initiative for Cycling Infrastructure (BICI) ኢንቨቲቭ አሸናፊ ከሆኑ አስር የዓለማችን ከተሞች ውስጥ አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply