ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለፀ።

ትራንስፖርት ቢሮ (ግንቦት 25/2015 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከሰጠው ህጋዊ ታሪፍ ውጭ በማስከፈል እንዲሁም መስመር በማቆራረጥ፣ የትራፊክ ምልክቶችን ባለከበሩና ከካራ እስከ ለምበረት ያለውን ለአውቶብስ ብቻ በተፈቀደ መንገድ በሚያሽከረክሩ 46 የባጃጅና 160 የሚኒባስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ የካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ።

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠርና ቢሮው ከሰጠው ህጋዊ ታሪፍ ውጪ የሚያስከፍሉ ህገ- ወጥ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃው እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።

አገልግሎት አሰጣጡንም የተሻለ ለማድረግ የካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከትራፊክ ማኔጀመንት ኤጀንሲ፣ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት፣ ከክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበ፣ ከፖሊስ መምሪያ፣ ንግድ ፅህፈት ቤት፣ ወንጀል መከላከል፣ ህብረተሰብ አቀፍ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ ሰላምና ጸጥታና ትራፊክ ፖሊስ ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር መሆኑን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ አሳውቆል።

በመጨረሻም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ቢሮው ባስቀመጠው ህጋዊ ታሪፍ ብቻ መስጠት እንደሚገባቸው ቢሮው ያሳስባል።

Leave a Reply