ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን ከማዘጋጃ ቤት በቴዎድሮስ አደባባይ ቸርችል ጎዳና እና ከወሎ ሰፈር እስከ ኡራኤል ባለው መንገድ ተከናወነ

(መስከረም 22/2015 ዓ.ም) ‘መንገድ ለሰው’ በሚል ስያሜ ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን ከማዘጋጃ ቤት በቴዎድሮስ አደባባይ ቸርችል ጎዳና ላይ እና ከወሎ ሰፈር እስከ ኡራኤል ባለው መንገድ ላይ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ በተለያዩ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች ተከናውኖ ተጠናቀቀ፡፡

በስፖርታዊ ፕሮግራሙ ላይ የብዙሃን የእግር ጉዞ እና የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፣ የብስክሌት መንዳትና ልምምድ እንዲሁም ስኬቲንግ፣ ሩጫ፣ የጎዳና ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ኤሮቢክስ፤ በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን አላማ ያደረገው ሞተር አልባ እንቅስቃሴ በማበረታታት የትራፊክ አደጋ የማይከሰትባት ከተማ መፍጠር፣ ለኑሮ ምቹና ከብክለት የፀዳ ከባቢ አየር እንዲኖር ማድረግ እንደ አጠቃላይ ጤናማ የአኗኗር ዘዴን በመፍጠር አማራጭ የትራንስፖርት መንገድ ለማበረታታት ነው።

@TMA

Leave a Reply