ከተረጅነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ፤ በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ መሆን እንደሚገባ ተገለፀ።

(የትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 27/2016ዓ.ም) አዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ሰራተኞች ከተረጅነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር በሚል በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

የውይይቱን ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው ኃላፊ አማካሪ አቶ ጆኒ ተረፈ የሰነዱ ዋና ዓላማ በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጅነትና ልመና እና አስተሳሰብ በማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ የምርታማነት ደረጃ ማሸጋገር እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ሰራተኛውን ያወያዩት የቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችም ልመናና የተረጂነት አስተሳሰብን ማስወገድ እንደሚገባ፣ ሁለንተናዊ ክብርና ሉኣላዊነትን የማስከበር ተልዕኮ እንዲሁም የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህልን ማጠናከር እንደሚገባና ይህንንም ወደ ተግባር ለመቀየርና በብቃት ለመፈፀም በየደረጃው ኮሚቴ መዋቀሩን ገልፀዋል።

በመጨረሻም በትራንስፖርት ዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችም በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ከድህነትን ለመላቀቅ በተባበረ ክንድ መስራት እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተጠቁሟል።

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply