ከተማዋ የትራፊክ እንቅስቃሴ ፍሰትን ያወኩ እና የትራፊክ ህጎችን የጣሱ ከ2ሺህ የሚበልጡ አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ተወሰደ

*************************

(ግንቦት 29 /2016 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ11ዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት በተለይም በኮሪደር ልማቱ አከባቢዎችና በስራ መግቢያ መውጪያ ሰዓቶች ባካሄደው የተጠናከረ ቁጥጥር የትራፊክ ደንብ የጣሱ 2,798 አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ወስዷል፡፡

ባልስልጣን መ/ቤቱ በቁልፍ የደህንነት ህጎችን ከማስከበር እና የትራፊክ ፍሰት ከማሳለጥ አንፃር ግንቦት 26 እና 27/2016 ዓ.ም በሁለት ቀናት ውስጥ በተለይም በስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ለአውቶቡስ ብቻ በተሰመረ መስመር ያሽከረከሩ፤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ፣ ሞባይል እያነጋገሩ ያሽከረከሩ፣ የደህንነት ቀበቶ እና የራስ ቆብ መከላከያ ሳያደርጉ የተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተገልጽዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በመዲናዋ የትራክ ፍሰቱ እንዲሳለጥ ብሎም ለከተማው ማህበረሰብ ደህንነት ማስጠበቅ ሲል የሚሰራ የህዝብ ተቋም ከመሆኑ አንፃር በቀጣይም መሰል ችግሮችን እየተቆጣጠረ የእርምት እርምጃ የሚወስድ ሲሆን በተለይም በህዝብ ሃብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶች ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ እንዲበላሹ የሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ በድጋሚ እየገለጸ አሽከርካሪዎችም ይህን አውቀው በሃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ ያሳስባል፡፡

@TMA

Leave a Reply