ከቦሌ ዓለም ህንፃ እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ 4.4 ኪ.ሜ መንገድ ግንባታ በቅርቡ ሊጀመር ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ጥር 05፤ 2015 ዓ.ም፤ ከቦሌ ዓለም ህንፃ እንግሊዝ ኤምባሲ 4.4 ኪሜ መንገድ ግንባታ በቅርቡ ሊጀመር መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ፡፡

ቢሮው በፕሮጀክቱ አተገባበር ዙሪያ የቅድመ-ዝግጅት እና ትግበራ ምዕራፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦሌ ጁፒተር ሆቴል ምክክር አድርጓል፡፡

በቢሮው የትራንሲፕ ፕሮጀክቶች ትግበራ ኃላፊ ኢንጂነር ትንሳኤ ወ/ገብርኤል እንደተናገሩት የመንገድ ፕሮጀክቱ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልፀዋል፡፡

ስለሆነም ለፕሮጀክቱ መሳካት የባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰቡ ሚናና ባለቤትነት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ተደጋጋሚ ውይይቶች መደረጋቸውን ኢንጂነር ትንሳኤ አመላክተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ….

ዘገባው፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

ለበለጠ መረጃ፦ በፕሮጀክቱ ዙሪያ ሃሳብ አስተያየት ያላችሁ በአካል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 እና 8 በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እና 4 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በመቅረብ ወይም በነፃ የስልክ መስመር 9620 በመደወል ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

Leave a Reply