ከሚያዚያ 16 2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ይሆናል ተባለ።

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይቱ የሙከራ ማስጀመሪያ ከኢትዮ ቴሌክም ጋር ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን ከሚያዚያ 16 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግን በአዲስ አበባ ባስገዳጅ ሁኔታ ይጀመራል ተብሏል።

በሌሎች ክልሎች ደግሞ ከግንቦት 1 ጀምሮ እንደሚጀመር ተገልፃ የኩፖን ተጠቃሚዎች ከሐምሌ 1 2015 ጀምሮ ግዴታዉ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ይህንንም ሲሰተም የሚቆጣጠር አንድ ማዕከል መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ምን ያህል ሽያጭ እንደተደረገ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ መረጃ የሚሰጥ መሆኑ ተገልፃል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ዉጬ ለሌሎች ባንኮችም የኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይቱን ይቀላቀላሉ ተብሏል።

Leave a Reply