“ኑ የጋራ ቤታችንን እንገንባ !!”

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በጋራ ያዘጋጁት “ኑ የጋራ ቤታችንን እንገንባ !!” በሚል መሪ ቃል የወጣቶች የፓናል ውይይት በካፒታል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ዛዲግ አብርሃ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አስተባባሪ ሚኒስትር፣ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ አቶ አበበ አካሉ ከኢዜማ እና አቶ ይህዓለም ታምሩ ከአብን ሲሆኑ የፓናል ውይይቱን ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ በአወያይነት እየመሩት ይገኛሉ ፡፡

በፓናል ውይይቱ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply