ትራንስፖርት ቢሮው ከሰጠው ህጋዊ የስምሪት መስመር ውጪ አገልግሎት በሚሰጡ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

ትራንስፖርት ቢሮ (ግንቦት 24/2015ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮልፌ ቀራኒዮና የልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በጋራ በመሆን በህገ ወጥ መንገድ ከቢሮው እውቅና ውጪ አዲስ የስምሪት መስመር በመክፈት የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ በሆኑ 49 የሚኒባስ ታክሲ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ፡፡

ተሸከርካሪዎቹ ከአለም ባንክ በአየር ጤና ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ ሲገባቸው ከአለም ባንክ በቤተል በመንዲዳወደ ጦር ኃይሎች እየጫኑ ህብረተሰቡን ለእንግልት እንደዳረጉህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ባደረገው ክትትል መሆኑን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶቹ ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply