ተቋማት የሴቶችን፣ የህፃናትን፣ የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋውያንን ጉዳይ በእቅዳቸው አካተው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15፤ 2015 ዓ.ም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የስርዓተ-ፆታ እና ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች፤ ከከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ለቢሮና ቅርንጫፍ አመራሮች እና ሠራተኞች ስልጠና ተሰቷል፡፡

ለከተማ ብሎም ለአገር እድገት የእነዚህ ልዩ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ሚና የጎላ መሆኑ የተመላተ ሲሆን ተቋማት በእቅዳቸው አካተው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ስልጠናው በዋናነት የትራንስፖርት ዘርፉ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመደበኛ ስራዎቹ የሴቶችን፣ ህፃናትን፣ የአካል ጉዳተኞችን የአረጋውያንን በጥቅሉ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ በእቅዳቸው አካተው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡

በቢሮው የስርዓተ-ፆታና ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተወካይ ወ/ሮ ብዙዓለም ገበየሁ እንደተናገሩት እነዚህን ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳይ ሁሉም አካል በትኩረት ሊመለከተውና ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ወ/ሮ ብዙዓለም ከተማ አስተዳደሩ በተለይ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ይህንን የሚመራና የሚያስተባብር መዋቅር በየተቋማት ሊያደራጅ እንደሚገባም ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ከሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የግንዛቤ ስርፀትና ንቅናቄ ቡድን መሪ ወ/ሮ አየሁ ደመቀ በበኩላቸው በስልጠናው ወቅት እንዳነሱት ተቋማት የሴቶችን፣ የህፃናትን፣ የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋውያንን ጉዳይ በእቅዳቸው አካተው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ገለፀዋል፡፡

ሰልጣኞችም እንደስራቸው የተግባር ባህሪ በየእቅዳቸው አካተው በየቀኑ የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ ጉዳያችን ብለው ሊመለከቱ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በአቅም ማጎልበቻውም የትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች፣ እና የቢሮው ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘገባው፡-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-3374 ወይም ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply