“ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ቃል በከተማችን የብክለት መከላከል ንቅናቄ ባስጀመርንበት እለት ከ150 በላይ በኤክትሪክ የሚሰሩ በሃገራችን የተመረቱ ሚኒባስ መኪናዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ተቋማት አስተላልፈናል::

በከተማችን ዘመኑ የሚጠይቀውን ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ ተቋሞቻችንን በቴክኖሎጂ እና የተለያዩ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም በማብቃት ላይ እንገኛለን::

በአንድ በኩል መሰረተ ልማት እየዘረጋን በሌላ በኩል የአየር ብክለትን እና ሙቀትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎትን እያሳለጥን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ የመገንባት ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Leave a Reply