በአዲሱ የሪፎርም አደረጃጀት የተመደቡ ሰራተኞች በተመደቡበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ ጀመሩ

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ባደረገው አዲስ የሪፎርም አደረጃጀት መነሻነት ዛሬ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የተመደቡ ሰራተኞች ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

የቦሌ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎች ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ህብረተሰቡ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ በተመደቡበት የስራ ቦታ እያገለገሉ ይገኛሉ።

ህብረተሰቡም ቢሮው ካስቀመጠው ህጋዊ ታሪፍ ተመን በላይ ባለመክፈልና ህገወጥ አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥመው በአከባቢው ለሚገኝ የትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎች፣ ለትራፊክ ፖሊስና በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ እንዲሰጡ ቢሮው ያሳውቃል።

Leave a Reply