በትናንትናው እለት ወደ ስራ የገቡት 100 የከተማ አውቶብሶች ልዩና ዘመናዊ የሚያደርጋቸው

በሀይገር ካምፓኒ የተመረቱና ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ አቅራቢዎች መቅረብ መቻሉ

🔺ለአካል ጉዳተኛ በልዩ ሁኔታ አጋዥ ሆነው የተሰሩ እና ዊልቸር ተጠቃሚ ለሆኑ የሚልቸር ማቆሚያ (ማሰሪያ) ያላቸው መሆኑ

🔺በቴክኖሎጂ ቁጥጥር ለማድረግ ሲስተም የተገጠመላቸው መሆኑ

🔺ተሳፋሪን ለመጫን ሲቆሙ ከመሬት ወለል ዝቅ ብለው ምቹ በሆነ መልኩ የሚጭኑ

🔺ርዝመታቸው 12 ሜትር ፣ ቁመቱ 3.4 ሜትር እንዲሁም ስፋታቸው 2.5 ሜትር ነው

🔺40 ሰው በወንበርና 30 ሰው ያለ ወንበር በድምሩ 70 ሰው በተንደላቀቀ ሁኔታ የመያዝ አቅም ያለው

🔺እንደየመንገዱ ባህሪ (ሁኔታ) ዝቅ እና ከፍ እያሉ የተሳፋሪን ምቾት ጠብቀው የሚጓዙ

🔺ተሳፋሪ በጉዞ ላይ እያለ የUSB PORT (ሞባይል ቻርጅ) ማድረግ የሚያስችል ሲስተም አለው

🔺የቻንሲ አካላት (ካንቢዎ፣ ሞተርና ኤርባግ ) በቀላሉ እንዳይጎዳ ጠንካራ ብረት የተገጠመላቸው

🔺ተሳፋሪዎች በድምፅ የደረሱበትን ቦታ መረጃ የሚሰጡ

🔺አውቶብሶቹ ሙሉ በሙሉ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ

🔺 የተሳፋሪውን እንቅስቃሴና ደህንነት በካሜራ መቆጣጠር የሚችል

🔺የሞተር ሙቀትን የመከላከል አቅም ፋን (ማቀዝቀዣ) የተገጠመላቸው መሆኑ ልዩና ፍፁም ዘመናዊ ያደርጋቸዋል

Leave a Reply