በትራንስፖርት አገልግሎት ማሻሻያ እና በሌሎች ስትራቴጂክ ጉዳዮች ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ውይይት አደረጉ።

ከንቲባ አዳነች ከዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ኦስማን ዲዮን ጋር ነው ውይይት ያደረጉት ::

በውይይታቸው ስትራቴጂካዊ በሆኑ በተቋማዊ ግንባታ፣ የከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓቱን የማሻሻል፣ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን ማዘመን፣ #የትራንስፖርት_አገልግሎት_ማሻሻል እንዲሁም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ በመሳሰሉት ጉዳዮችን ነው የተወያዩት::

ከንቲባ አዳነች የዓለም ባንክ በእነዚህ ወሳኝ መስኮች ለሚያደርገው ድጋፍ በከተማው ነዋሪ ስም አመሰግነዋል።

Leave a Reply