(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣንና ከከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመቀናጀት በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሚታየውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል።
ቢሮውም የመልካም አስተዳደር በሚስተዋሉባቸው ተርሚናሎችና መስመሮች የቢሮ ኃላፊውን ጨምሮ የቢሮው አመራሮች ድጋፍና ክትትል በሚያደርጉባቸው ቦታዎች በስራ መግቢያና መውጫ በመገኘት እየደገፉ ይገኛሉ።
ድጋፍ እየተደረገባቸው ባሉ መስመሮች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር ጊዚያዊ ስምሪት በመስጠት፣ ተጨማሪ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችንና የክልል አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ድጋፍ እንዲሰጡ በማድረግ፤ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት እየተሰጠ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል።
የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የሚስተዋለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
ህብረተሰቡም ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው አስተያየትና ጥቆማ በ 9417 ነጻ የስልክ መስመር ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ቢሮው ይገልፃል።