ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናካር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ

(መጋቢት 30/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡- በትራፊክ አደጋ በሃገራችን በአማካኝ በዓመት ከ5‚000 በላይ የሞት አደጋ የሚመዘገብ ሲሆን በከተማችን አዲስ አበባ ደግሞ በአማካይ ከ450 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን ያጣሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በከተማችን የምስተዋለውን የመንገድ ደህንነት ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ ስራዎችን የመገምገሚያ መድረክ አዘጋጀ።

በያዝነው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ስራዎችን ካባለድርሻ ተቋማት ጋር በመገምገም ቅንጅተታዊ አሰራርን በማጠናከር በቀሪው የበጀት ዓመት ወራት የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም፣ የባለድርሻ ተቋማት ሚና እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በኤጀንሰው የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር እና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጌታቸው ሰነድ ቀርቧል።

የውይይት መድረኩን የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አካሉ አሰፋ እና የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ አማረ ታረቀኝ እና ኢንጂነር ኤሊያስ ዘርጋ መርተውታል።

ከባለድርሻ ተቋማት በመድረኩ የተሳተፉ ኃላፊዎች በአፈፃፀም ላይ በዘጠኝ ወሩ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ከትራፊክ አደጋ ለመታደግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በውይይት መድረኩ ከትራንስፖርት ቢሮ፣ ከአዲስ ከበባ ፖሊስ ኮምሽን፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከንግድ ቢሮ፣ ከትምህርት ቢሮ፣ ከጤና ቢሮ፣ ከአዲስ ከበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከብሉምበርግ ኢኒሺየቲቭ እንዲሁም ከኤጀንሲው የቅርንፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች እና ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አካሉ አሰፋ ባለድርሻ ተቋማት ለከናወኑት ስራ አመስግነው የሰው ልጅ ህይወት እና አካል እንዲሁም ንብረትን ከውድመት ለማዳን በሚደረግ ርብርብ ላይ እና በከተማችን ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን እንዲሰራና እንዲረባረብ በመጠየቅ በቀጣይም በተመሳሳይ መድረክ ተገናኝተን ስራዎቻችንን እንገመግማለን ብለዋል፡፡

@TMA

Leave a Reply