ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖ ሊመረቅ ነው፡፡

ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖ ሊመረቅ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6፤ 2012 ዓ.ም፤በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖን ግንቦት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ ሊያስመርቅ ነው፡፡

ለዴፖው ግንባታ 789.5 ሚሊዮን ብር በጀት ወጪ ተደርጎበታል፡፡

የምረቃ ስነ ስርዓቱ ቃሊቲ አካባቢ በተገነባው የአውቶቡስ ዴፖ ቅጥር ግቢ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ይከናወናል፡፡

በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን በተመቻቸ ሁኔታ የማቆም አቅም ያለው ይህ ዴፖ 89 አውቶቡሶችን ከመሬት በታች ማቆም ያስችላል፡፡

ዴፖው በዉስጡ ዘመናዊ ጋራዥን ጨምሮ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎችን ያካተተ ከአንድ ማዕከል ሥምሪት የሚሰጥበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው፡፡

በተጨማሪም ሁለት የአውቶቡስ ማጠቢያ ማሽንና አራት የነዳጅ መቅጃ ማሽን ያለው ነዳጅ ማደያ እና በአንዴ ለ19 አውቶቡሶች የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ዴፖ መሆን ችሏል፡፡

የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም የመቀባት አገልግሎት መስጠት የሚችል ዘመናዊ የአውቶቡስ ዴፖ ነው፡፡

ከዚህም በላይ አንድን አዉቶቡስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ አጥቦ የሚያደርቅ ቴክኖሎጂ ባለቤትም ነው፡፡

ዴፖው ሲኤስሲኢ በተባለ የቻይና የግንባታ ተቋራጭ የተገነባ ሲሆን፥ የማማከር ስራው ደግሞ ኢቲጂ በተባለ ዲዛይነርና ማማከር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ተከናውኗል፡፡

Leave a Reply