“ስምምነቱ የመላ ህዝባችንን ፍላጎት የሚያሟላና ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ ነው” – ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የሰላም ስምምነቱ ህገ መንግስታዊ ስርአቱንና ብሄራዊ ጥቅማችንን ባስከበረ መልኩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።

ስምምነቱ መንግስት ካስቀመጠዉ አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ፣ የመላ ህዝባችንን ፍላጎት የሚያሟላ፣ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥና የትግራይን ህዝብ መሠረታዊ ችግሮች የሚፈታ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።

ወደዚህ ድል የደረስነው መላው የፀጥታና የደህንነት ሃይሎቻችን በከፈሉት መስዋእትነትና በመሬት ላይ ባስመዘገቡት ድል፣ ህዝባችን አንድ ሆኖ በመቆሙና መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ ባሳየው ቁርጠኝነት ነው ብለዋል።

ድሉ የመላ ኢትዮጵያውያን ድል ነው፤ አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ናት ነው ያሉት ዶ/ር ለገሰ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባጋሩት ፅሁፍ።

Leave a Reply