መረጃ

ከ1968 እስከ የካቲት 2015ዓ/ም የቤት ግብር ሲከፍሉ የነበሩ 182 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች ላለፉት 45 ዓመታት በባለቤትነት ለያዙት ቤት በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ግብር ሲከፍሉ ቆይተዋል::

የከተማ ቦታ ለክፍያ እንዲያመች ሲባል በሶስት ደረጃዎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም አንደኛ ደረጃ ፣ ሁለተኛ ደረጃ እና ሶስተኛ ደረጃ ተብለው ተለይተዋል::

1. ለመኖሪያ ቤት የተያዘ የከተማ ቦታ ኪራይ ተመን:-

– የቦታ መጠኑ በካሬ ሜትር እስከ 500 ለሆነ በአንደኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.06 ሳንቲም ፣ በሁለተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.04 ሳንቲም እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በካሬ ሜትር 0.02 ሳንቲም ነበር::

– የቦታ መጠኑ በካሬ ሜትር ከ501 – 1000 ለሆነ በአንደኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ በአንድ ካሬ 0.08 ሳንቲም ፣ በሁለተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.06 ሳንቲም እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በካሬ ሜትር 0.04 ሳንቲም ነበር::

– የቦታ መጠኑ በካሬ ሜትር ከ1501 – 2000 ለሆነ በአንደኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.13 ሳንቲም ፣ በሁለተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.10 ሳንቲም በሶስተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በካሬ ሜትር 0.07 ሳንቲም ነበር::

– የቦታ መጠኑ በካሬ ሜትር ከ2001 በላይ ለሆነ በአንደኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.16 ሳንቲም ፣ በሁለተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በአንድ ካሬ 0.14 ሳንቲም እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በካሬ ሜትር 0.12 ሳንቲም ነበር::

2. ለመስሪያ ቦታ/ ለንግድ የተያዘ ቦታ የክፍያ ተመን

– በአንደኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በእያንዳንዱ ካሬ ሜትር 0.06 ሳንቲም በሁለተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በእያንዳንዱ ካሬ 0.04 ሳንቲም በሶስተኛ ደረጃ የተመደበ ቦታ ክፍያ በእያንዳንዱ ካሬ 0.02 ሳንቲም ነበር::

3. ተጨማሪ መረጃዎች

– በከተማችን ካሉ ከ800 ሺህ በላይ የቤት ባለቤቶች ከላይ የተጠቀሰውን የክፍያ ተመን ሲከፍሉ የነበሩት 182 ሺህ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው::

– የከተማ አስተዳደሩ በ1968 የከተማ ቦታ መጠቀሚያ ኪራይ እና የቤት ግብር ለማስከፈል ካወጣው ደንብ ያሻሻለው የዋጋ ተመኑን ብቻ ነው:: ተመኑም የወቅቱን የቤት ዋጋ እና የገበያ ተመን በጥናት በማስደገፍ የተደረገ ማሻሻያ ነው::

– እስከ አሁን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች የቤት ግብራቸውን የከፈሉ ሲሆን በከተማችን ትላልቅ ህንፃ እና ቅንጡ ቤት ያላቸው ነዋርዎች ከሌሎቹ አንፃር ሲታይ ክፍያቸውን እየፈፀሙ አይደለም:: ስለዚህ ክፍያው ይቁም ቢባል እንኳን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ስለከፈሉ ከክፍያው የሚያመልጠው ከፍተኛ ገቢ ያለው የከተማችን ነዋሪ ነው::

– ለከተማችን ነዋሪዎች ከየካቲት 2015 ዓ/ም ጀምሮ የተሻሻለውን የክፍያ ታሪፍ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል::

Leave a Reply