ህገወጥ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን የአዲስ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም)

የአዲስ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክፍለከተማው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባለ 3 እና ባለ 4 እግር (ባጃጅ) ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ከክፍለከተማው ትራፊክ ፖሊስና ፖሊስ ጋር በማቀናጀት ህገወጥ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል።

የአዲስ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ በላይነህ ተሻገር ከስምሪት መስመር ውጭ በሚሰሩ፣ አስፖልት የሚያሽከረክሩ፣ የመስመር ታፔላ የሌላቸውና ከተቀመጠው ታሪፍ በላይ በማስከፈል የመልካም አስተዳደር ችግር በፈጠሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በሁለት ቀናት በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ 28 አሽከርካሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን፤ 15 ባጃጆች የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው በመሆኑ ፖሊስ እርምጃ የሚወስድባቸው እንደሚሆን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ያሳውቃል።

Leave a Reply