“የአዲስ ዓመት ስጦታ ለእናት ሀገሬ”

“የአዲስ ዓመት ስጦታ ለእናት ሀገሬ”

“አዲስ ዓመት ለእናት ሀገሬ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የስጦታ ፕሮግራም ለመደገፍ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እና የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሚሊኒየም አዳራሽ ስጦታውን አስረክበዋል፡፡

“የአዲስ ዓመት ስጦታ ለእናት ሀገሬ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የአዲስ አመት ስጦታ እውን ለማድረግ የተለያዩ ስጦታዎች ርክክብ ተካሄደ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የአዲስ አመት የስጦታ መርሀ ግብር መሰረት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ታከለ ሉሌና እና የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰመረ ጀላሎ በቦታው በመገኘት የርክክብ ስነ ስርዓቱ ተከናውኗል፡፡

በዕለቱ በቁጥር 99 አልባሳትና ጫማ፣ 10 ደርዘን ደብተር፣ 38 እስክርቢቶ፣ እርሳስና መቅረጫ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ተበርክቷል፡፡

Leave a Reply